Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 14:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ስለዚህ ነገር የሙታንንና የሕያዋን ጌታ እንዲሆን ክርስቶስ ሞቷልና፥ ሕያውም ሆኖአልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ለዚሁ፣ የሙታንና የሕያዋን ጌታ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ ሞቷል፤ በሕይወትም ተነሥቷል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ስለዚህ ክርስቶስ ሞቶ ከሞት የተነሣው የሕያዋንና የሙታን ጌታ ለመሆን ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ስለ​ዚህ ሕያ​ዋ​ን​ንና ሙታ​ንን ይገዛ ዘንድ ክር​ስ​ቶስ ሞተ፥ ተነ​ሣም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ስለዚህ ነገር ሙታንንም ሕያዋንንም ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞቶአልና ሕያውም ሆኖአልና።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 14:9
20 Referencias Cruzadas  

ሕያውም እኔ ነኝ፤ ሞቼም ነበርሁ፤ እነሆም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።


ክርስቶስ ይህን መከራ መቀበልና ወደ ክብሩ መግባት ይገባው የለምን?”


የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።


በእግዚአብሔር ፊት፥ በሕያዋንና በሙታንም ላይ በሚፈርደው በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም አጥብቄ አዝዝሃለሁ፤


ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።


ነገር ግን በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው ለእርሱ መልስ ይሰጡበታል።


እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሞት ባስነሣው ክብርንም በሰጠው፥ በእግዚአብሔር በእርሱ ትተማመናላችሁ።


አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ እርግጠኞች በመሆናችን፥ የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል፤ ይህ በመሆኑም ሁሉ ሞተዋል።


የሁሉ ጌታ በሚሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እየሰበከ ይህን ቃል ወደ እስራኤል ልጆች ላከ።


“በሰምርኔስም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ ሞቶ የነበረው፥ ሕያውም የሆነው፥ ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦


እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።


ምክንያቱም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፥ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ፤


ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም ደግሞ በኢየሱስ በኩል ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋል።


የምንነቃም ብንሆን፥ የምናንቀላፋም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንድንኖር ስለ እኛ ሞተ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios