ሮሜ 14:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን ጌታ ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌላውን በሚያገለግል ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? እርሱ ቢወድቅ ወይም ቢቆም ለጌታው ነው፤ ጌታ ሊያቆመው ስለሚችልም ይቆማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ በሌላ ሰው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ የጌታው ጉዳይ ነው። እንዲያውም እግዚአብሔር ሊያቆመው ስለሚችል ጸንቶ ይቆማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ የሌላውን ሎሌ የምትነቅፍ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለጌታው ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያነሣው ይችላልና ይቆማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል። |
እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመነው ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን ያን ስጦታ ለእነርሱ ከሰጠ፥ እግዚአብሔርን ለመከላከል እችል ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ?”
ነገር ግን፥ ሰው ሆይ! ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? የተሠራ ነገር የሠራውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ይለዋልን?