Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 14:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ታዲያ፥ በሌላ ሰው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ የጌታው ጉዳይ ነው። እንዲያውም እግዚአብሔር ሊያቆመው ስለሚችል ጸንቶ ይቆማል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሌላውን በሚያገለግል ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? እርሱ ቢወድቅ ወይም ቢቆም ለጌታው ነው፤ ጌታ ሊያቆመው ስለሚችልም ይቆማል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን ጌታ ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እን​ግ​ዲህ የሌ​ላ​ውን ሎሌ የም​ት​ነ​ቅፍ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወ​ድቅ ለጌ​ታው ነው። ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ነ​ሣው ይች​ላ​ልና ይቆ​ማል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 14:4
19 Referencias Cruzadas  

አንተ ሰው! ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ምን መብት አለህ? የሸክላ ዕቃ ሠሪውን “ለምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ?” ሊለው ይችላልን?


እንዳትወድቁ ሊያደርጋችሁና ነቀፋ የሌለባችሁ አድርጎ በደስታ በክብሩ ፊት ሊያቀርባችሁ ለሚችል፥


እግዚአብሔር በእጁ ስለሚደግፈው ቢደናቀፍም አይወድቅም።


ስለዚህ እነርሱን ለማማለድ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእርሱ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ በፍጹም ሊያድናቸው ይችላል።


ስለዚህ ማንኛውንም ነገር የሚበላ ሰው የማይበላውን ሰው አይንቀፈው፤ የማይበላውም በሚበላው ሰው ላይ አይፍረድ፤ እርሱንም እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።


እኔ በማበሥረው የምሥራች ቃል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚተላለፈው መልእክትና ከጥንት ዘመን ጀምሮ ተደብቆ በቈየው፥ አሁን ግን በተገለጠው የእውነት ምሥጢር አማካይነት እርሱ በእምነታችሁ እንድትቆሙ ሊያደርጋችሁ ይችላል።


እርሱ ለደከሙት ብርታትን ይሰጣል፤ ለዛሉትም ኀይልን ይጨምራል።


እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድን ይወዳል፤ ታማኞቹንም አይተዋቸውም፤ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል፤ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።


ዘወትር በመንገድህ ተራመድኩ፤ ከመንገድህም ወጥቼ አልባዘንኩም።


እናንተም በመጨረሻው ቀን ለሚገለጠው መዳን በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኀይል ተጠብቃችኋል።


እኛ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመንን ጊዜ እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠውን ስጦታ ለእነርሱም ከሰጣቸው፤ ታዲያ፥ እግዚአብሔርን ለመከልከል የምችል እኔ ማን ነኝ!”


የክፉዎች ኀይል ይሰበራል ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ያበረታቸዋል።


አይሁድ አለማመናቸውን ቢያስወግዱ ወደ ቀድሞው ቦታቸው ይመለሳሉ፤ እግዚአብሔር ወደ ቀድሞው ቦታቸው ሊመልሳቸው ይችላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios