ሮሜ 13:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ምክንያት ደግሞ ግብር ትከፍላላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግብር የምትከፍሉትም ደግሞ ለዚህ ነው፤ ባለሥልጣናቱ፣ በዚሁ ተግባር ላይ የተሰማሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግብር የምትከፍሉትም ስለዚህ ነው፤ ባለሥልጣኖች በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩት እግዚአብሔርን ለማገልገል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ግብር ታገቡላቸዋላችሁ፤ ለዚህ ሥራ የተሾሙ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ደግሞ ትገብራላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና። |
አሁንም ይህች ከተማ ከተገነባች፥ የቅጥሮቿም ሥራ ከተጠናቀቀ፥ ግብርና ቀረጥ መጥንም እንዳይሰጡ፥ ንጉሡንም እንደሚጎዳ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን።
ይህን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲሠሩ ለአይሁድ ሽማግሌዎች የምታደርጉትን አዝዣለሁ፥ በወንዝ ማዶ ካለው አገር ከሚመጣው ግብር ከንጉሡ ገንዘብ ለእነዚህ ሰዎች ወጪውን በትጋት ይሰጣቸው፥ ሥራም እንዳታስፈቱአቸው።
“ይህ ሕዝባችንን ሲያስት ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል፥ ደግሞም ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ፤’ ሲል አገኘነው” ብለው ይከሱት ጀመር።