ሮሜ 10:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል፥ በአፉም መስክሮ ይድናልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትጸድቀው በልብህ አምነህ ነው፤ የምትድነውም በአፍህ መስክረህ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው በልቡ ሲያምን ይጸድቃል፤ በአፉም ሲመሰክር ይድናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልቡ የሚያምን ይጸድቃልና፤ በአፉም የሚመሰክር ይድናልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። |
ሆኖም ሰው የሚጸድቀው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ በሕግ ሥራ እንዳልሆነ አውቀን፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ በማመን እንድንጸድቅ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል። ሥጋ ሁሉ በሕግ ሥራ አይጸድቅም።
በክርስቶስም በማመን በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ እንጂ በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴ ጽድቅ ሳይኖረኝ፥ በእርሱ እንድገኝ ነው፤
“የት እንደምትኖር አውቃለሁ፥ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ነው፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።