Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በልቡ የሚ​ያ​ምን ይጸ​ድ​ቃ​ልና፤ በአ​ፉም የሚ​መ​ሰ​ክር ይድ​ና​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የምትጸድቀው በልብህ አምነህ ነው፤ የምትድነውም በአፍህ መስክረህ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል፥ በአፉም መስክሮ ይድናልና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሰው በልቡ ሲያምን ይጸድቃል፤ በአፉም ሲመሰክር ይድናል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 10:10
13 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።


ኢየ​ሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአ​ፍህ ብት​መ​ሰ​ክር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ እንደ አስ​ነ​ሣው በል​ብህ ብታ​ምን ትድ​ና​ለህ።


ሰው በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በማ​መን እንጂ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት እን​ደ​ማ​ይ​ጸ​ድቅ እና​ው​ቃ​ለ​ንና፤ እኛም የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት ሳይ​ሆን በእ​ርሱ በማ​መ​ና​ችን እን​ጸ​ድቅ ዘንድ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አም​ነ​ናል፤ ሰው ሁሉ በኦ​ሪት ሥራ አይ​ጸ​ድ​ቅ​ምና።


እን​ግ​ዲህ ከክፉ ሕሊና ለመ​ን​ጻት ልባ​ች​ንን ተረ​ጭ​ተን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም በጥሩ ውኃ ታጥ​በን በተ​ረ​ዳ​ን​በት እም​ነት በቅን ልብ እን​ቅ​ረብ።


በመ​ል​ካም ምድር የወ​ደ​ቀው ግን ቃሉን በበ​ጎና በን​ጹሕ ልብ የሚ​ሰ​ሙና የሚ​ጠ​ብ​ቁት፥ ታግ​ሠ​ውና ጨክ​ነ​ውም የሚ​ያ​ፈሩ ናቸው።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ዕወቁ፤ ከእ​ና​ንተ ባንዱ ላይ ስንኳ ሃይ​ማ​ኖት የጐ​ደ​ለ​ውና ተጠ​ራ​ጣሪ፥ ከሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ያ​ችሁ ክፉ ልብ አይ​ኑር።


በእ​ር​ሱም እጸና ዘንድ፥ ዛሬ የኦ​ሪት ጽድቅ ሳይ​ኖ​ረኝ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገኝ ጽድቅ አለኝ እንጂ።


“የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።


ኢየሱስም “ቢቻልህ ትላለህ? ለሚያምን ሁሉ ይቻላል፤” አለው።


መጽ​ሐፍ፥ “የሚ​ያ​ም​ን​በት ሁሉ አያ​ፍ​ርም” ብሎ​አል።


ፊል​ጶ​ስም፥ “በፍ​ጹም ልብህ ብታ​ምን ይገ​ባ​ሃል” አለው፤ ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም መልሶ፥ “ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እኔ አም​ና​ለሁ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios