ራእይ 18:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኩሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኩሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በብርቱ ድምፅ እንዲህ ብሎ ጮኸ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ፣ የርኩሳን መናፍስት ሁሉ መጠጊያ፣ የርኩስና የአስጸያፊ ወፎች ሁሉ መጠለያ ሆነች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፍ ባለ ድምፅም እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ ሆነች! የርኩሳን መናፍስት ማደሪያ ሆነች! የሚያጸይፉና የሚያስጠሉ ወፎች መጠለያ ሆነች! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በብርቱም ድምፅ፦ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤ |
ስለዚህ እነዚህን ሁሉ ቃላት በእነርሱ ላይ ትንቢት ትናገራለህ፥ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ጌታ በላይ ሆኖ ይጮኻል፥ በቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል፤ በበረቱ ላይ እጅግ ይጮኻል፥ ወይንም እንደሚጠምቁ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል።
ጌታም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ያሰማል፥ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፥ ጌታ ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፥ ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።
መንጎችም የምድርም አራዊት ሁሉ በውስጧ ይኖራሉ፥ ጉጉትና ጃርት በዓምዶችዋ መካከል ያድራሉ፥ ድምፅም በመስኮት ይጮኻል፥ በመድረኩ ላይ ጥፋት ይደርሳል የዝግባ እንጨት ሥራ ይገለጣልና።
ሌላም መልአክ ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው “የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፤ የምድሪቱ መከር ደርሶአልና፤” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። የብርቱ ቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ እንዲሰጣትም ታላቂቱ ባቢሎን በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።
ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ውስጥ ፍርድሽ ይፈጸማልና፤” እያሉ ይናገራሉ።
አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንሥቶ እንዲህ ሲል ወደ ባሕር ወረወረው “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች፤ ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።