ራእይ 16:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚዛን ሲመዘን እያንዳንዱ አርባ ዐምስት ኪሎ ግራም የሚሆን ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ከበረዶው መቅሠፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ አርባ አምስት ኪሎ ግራም ያኽል የሚመዝን በረዶ ከሰማይ በሰዎች ላይ ወረደ፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበረ ሰዎች በበረዶው መቅሠፍት ምክንያት እግዚአብሔርን ተሳደቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሳ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፥ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነውና። |
እነሆ እኔ ነገ በዚህ ጊዜ በግብጽ፥ ከተመሠረተች ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ ሆኖ የማያውቅ፥ እጅግ ከባድ በረዶ አዘንባለሁ።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ በሰው፥ በከብት፥ በእርሻ ቡቃያ ሁሉ ላይ፥ በግብጽ ምድር ሁሉ በረዶ እንዲሆን እጅህን ወደ ሰማያት ዘርጋ።”
ጌታም ክቡር ድምፁን ያሰማል፥ የክንዱንም መውረድ በሚነድ ቁጣውና በምትበላ እሳት ነበልባል፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በበረዶ፥ ጠጠርም ይገልጣል።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመዓቴ በዐውሎ ነፋስ እሰነጣጥቀዋለሁ፥ በቁጣዬም ዶፍ ዝናብ፥ በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ሊያጠፋው ይወርዳል።
ከእስራኤልም ልጆች ፊት እየሸሹ የቤትሖሮንን ቁልቁለት በመውረድ ላይ ሳሉ፥ ዓዜቃ እስኪደርሱ ድረስ ጌታ ከሰማይ ታላላቅ ድንጋይ አወረደባቸውና ሞቱ፤ የእስራኤል ልጆች በሰይፍ ከገደሉአቸው ይልቅ በበረዶ ድንጋይ የሞቱት በለጡ።
በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በቤተ በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።
ሰዎችም በታላቅ ትኩሳት ተቃጠሉ፤ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሓ አልገቡም።
የፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።