ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
ራእይ 13:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎችም ለዘንዶው ሰገዱለት፤ ምክንያቱም ሥልጣኑን ለአውሬው ሰጥቶታል። ደግሞም፣ “አውሬውን የሚመስል ማን ነው? ከእርሱስ ጋራ ማን ሊዋጋ ይችላል?” በማለት ለአውሬው ሰገዱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአውሬው ሥልጣን በመስጠቱ ሰዎች ሁሉ ለዘንዶው ሰገዱለት፤ “አውሬውን የሚመስል ማን ነው? ከእርሱስ ጋር ማን ሊዋጋ ይችላል?” እያሉ ለእርሱም ሰገዱለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዘንዶውም ሰገዱለት፥ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም፦ አውሬውን ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት። |
ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
እንደ እነርሱ ከሆነ የማያምኑ ሰዎችን ልቦና፥ የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ አሳውሯል።
ስለ እነርሱም፥ ‘በዔናቅ ልጆች ፊት ማን መቆም ይችላል?’ ሲባል የሰማኸው፥ አንተም የምታውቃቸው፥ ግዙፍና ረጃጅም ሕዝቦች የዔናቅ ልጆች ናቸው።
እርሱም ሰው የሚያመልከውን ነገር ወይም አማልክት ነን ከሚሉት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግና በመቃወም፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ብሎ ያውጃል፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ ይቀመጣል።
በጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ከዚያም ዘንዶው ሴቲቱ በምትወልድበት ጊዜ ሕፃንዋን ለመዋጥ ልትወልድ በተቃረበችው ሴት ፊት ቆመ።
ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኀይሉን፥ ዙፋኑንና ትልቅ ሥልጣንን ሰጠው።
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉት የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ናቸው።”
በእነዚህም መቅሠፍቶች ያልተገደሉት የቀሩቱ ሰዎች ስለ እጃቸው ሥራ ንስሓ አልገቡም፤ ለአጋንንትና ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሠሩ ለጣዖቶችም መስገድን አልተዉም።