ራእይ 12:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አልቻላቸውምም፤ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ድል ተመቱ፤ በሰማይም የነበራቸውን ስፍራ ዐጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ዘንዶውና የእርሱ መላእክት ተሸነፉ፤ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አልቻላቸውምም፤ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም። |
በውኑ እኔን አትፈሩምን? ይላል ጌታ፤ ከፊቴስ አትደነግጡምን? አልፎት እንዳይሻገር አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ድንበር አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢናወጥ አያሸንፍም፥ ቢጮኽም አያልፈውም።
የመጀመሪያ ቦታቸውን ያልጠበቁትን ነገር ግን መኖሪያቸውን የተዉትን መላእክት በዘለዓለም እስራት እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ከጨለማ በታች ጠብቆአቸዋል።
ታላቁም ዘንዶ ወደ ታች ተጣለ፤ ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።