ባሕርና ሞላዋ፥ ዓለምም በእርሷም የሚኖሩ ይናወጡ።
ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ።
ባሕርና በውስጥዋ ያላችሁ ፍጥረቶች ሁሉ ድምፃችሁን አሰሙ፤ ዓለምና በእርስዋ የምትኖሩ ሁሉ ዘምሩ!
በደመና ዐምድም ተናገራቸው፤ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ።
የዳዊት መዝሙር። ምድርና ሞላዋ የጌታ ናቸው፥ ዓለምና በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ።
ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፥ ባሕርና ሞላዋ ይናወጡ፥
ጌታ ሕዝቡን አጽናንቶአልና፥ ለችግረኞቹም ራርቶአልና ሰማያት ሆይ፥ ዘምሩ፥ ምድር ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ተራሮችም ሆይ፥ እልል በሉ።
ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፥ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፥ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል።