የሕዝብ ደንቆሮች ሆይ፥ አስተውሉ፥ ሞኞችስ መቼ ጠቢብ ትሆናላችሁ?
እናንተ በሕዝቡ መካከል ያላችሁ ደነዞች፤ ልብ በሉ፤ እናንተ ሞኞች፤ ጥበበኞች የምትሆኑት መቼ ነው?
ከሕዝብ መካከል እናንተ አላዋቂዎች ይህን አስተውሉ፤ እናንተ ሞኞች ሆይ! አስተዋዮች የምትሆኑት መቼ ነው?
በምድረ በዳ እንደ ተፈታተኑትና እንዳስቈጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ።
ሰው ገና እንዲኖርና አዘቅቱንም እንዳያይ
እኔ የተናቅሁ ነኝ አላወቅሁምም፥ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
አቤቱ፥ ሥራህ እንዴት ትልቅ ነው! ሐሳብህም እንዴት ጥልቅ ነው!
“እናንት አላዋቂዎች፥ እስከ መቼ አላዋቂነት ትወድዳላችሁ? ፌዘኞችም ፌዝን ይፈቅዳሉ? ሞኞችም እውቀትን ይጠላሉ?
ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፥ እርማትን የሚጠላ ግን ሞኝ ነው።
እናንተ አላዋቂዎች፥ ማመዛዘንን ተረዱ፥ እናንተም ሞኞች አስተውሉ።
ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
በአንድ ጊዜ ቂላ ቂሎችና ሞኞች ሆነዋል፤ ጣዖታት የሚያስተምሩት ከግዑዝ እንጨት የማይሻልን ነገር ብቻ ነው።
የሚያስተውል የለም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም፤
አስተዋዮች ቢሆኑ፥ ይህንን በተገነዘቡ፥ ፍጻሜያቸውንም ባሰቡ ነበር!
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባርያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት ጊዜያችንን የምናሳልፍ፥ የምንጠላ፥ እርስ በርሳችንም የምንጠላላ ነበርን።