መዝሙር 86:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፥ ለቁጣ የዘገየህ፥ ጽኑ ፍቅርህና እውነትህ የበዛ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ ሆይ፤ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ ለቍጣ የዘገየህ፣ ምሕረትህና ታማኝነትህ የበዛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን መሐሪና ርኅሩኅ ለቊጣ የዘገየህ፥ የተትረፈረፈ ፍቅርና ታማኝነት ያለህ አምላክ ነህ። |
ለመስማትም እንቢ አሉ፥ በመካከላቸው ያደረግኸውን ተአምራት አላስታወሱም፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፥ በዓመፃቸውም ወደ ባርነታቸው ለመመለስ መሪ ሾሙ፤ አንተ ግን ይቅር ባይ አምላክ፥ ቸር፥ ርኅሩኅ፥ ለቁጣ የዘገየህና ምሕረትህ የበዛ ነህ፥ አልተውካቸውምም።”
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፥ ጌታ አምላካችሁም ቸርና መሐሪ፥ ቁጣው የዘገየ፥ ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።
ወደ ጌታ ጸለየ፥ እንዲህም አለ፦ “ጌታ ሆይ፥ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አስቀድሜ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል የፈለግሁትም ለዚህ ነበር፥ አንተ ቸርና ርኅሩኅ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ ከክፉ የምትመለስ አምላክ እንደሆንህ አውቄ ነበርና።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱን ትሩፍ ዓመጽ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ርኅራኄ ይወድዳልና ቁጣውን ለዘለዓለም አያቆይም።
‘ጌታ ታጋሽና ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ በደልንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን በደል እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው።’