ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፥ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።
የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ አድምጠኝ። ሴላ
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ! አድምጠኝ።
እግዚአብሔር አምላኬ የሚናገረኝን አደምጣለሁ፤ ሰላምን ለሕዝቡና ለጻድቃኑ፥ ልባቸውንም ወደ እርሱ ለሚመልሱ ይናገራልና።
ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥ እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።
ያለ በደል ሮጥሁ ተዘጋጀሁም፥ ተነሥ፥ ተቀበለኝ፥ እይም።
ጌታን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።
“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ በቂጣ በዓል፥ በመከርንና በዳስ በዓል፥ በአምላክህ በጌታ ፊት እርሱ በመረጠው ስፍራ ይታዩ፥ በጌታም ፊት ባዶ እጃቸውን አይታዩ።