የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ በሕዝብህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈጣለህ?
የእንባ እንጀራ አበላሃቸው፤ ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው።
ሐዘንን እንደ ምግብ፥ እንባንም እንደ መጠጥ በብዛት ሰጠሃቸው።
ወደ ግብፅ ሀገር በሄደ ጊዜ ለዮሴፍ ምስክርን አቆመ። የማያውቀውን ቋንቋ ሰማ።
ሰውነቴ ትነካው ዘንድ እንቢ አለችው፥ እንደሚያስጸይፍ መብል ሆነብኝ።
ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም በእኔ ስም ይራገማሉ።
ነፍሴ እግዚአብሔርን፥ ሕያው አምላክን ተጠማች፥ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?
የአሳፍ ትምህርት። አቤቱ፥ ስለምን ለሁልጊዜ ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቁጣህ ስለምን ጨሰ?
አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘለዓለም ትቈጣለህ? ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል?
ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፤ ዐይኖችህ ግን አስተማሪህን ያያሉ፥
ሳምኬት። በቁጣ ከደንኸን አሳደድኸንም፥ ገደልኸን፥ አልራራህም።
ጸሎት እንዳያልፍ ራስህን በደመና ከደንህ።