የጌታ መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ጌታ ስለ ክፉው ነገር አዘነ፤ ሕዝቡን የሚቀሥፈውንም መልአክ “ይበቃል! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
መዝሙር 78:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቁጣውን ንዳድ በላያቸው ሰደደ፥ መቅሠፍትን መዓትንም መከራንም በክፉዎች መላእክት ሰደደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽኑ ቍጣውን በላያቸው ሰደደ፤ መዓቱን፣ የቅናቱን ቍጣና መቅሠፍቱን ላከባቸው፤ አጥፊ የመላእክት ሰራዊትም ሰደደባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጥፋት መልእክተኞች ቡድን የሆኑትን አስፈሪውንና ኀይለኛ ቊጣውን፥ ማዋረዱንና ማስጨነቁን ላከባቸው። |
የጌታ መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ጌታ ስለ ክፉው ነገር አዘነ፤ ሕዝቡን የሚቀሥፈውንም መልአክ “ይበቃል! እጅህን መልስ” አለው። በዚያን ጊዜ የጌታ መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
ደሙም በምትኖሩባቸው ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብጽን ምድር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም።
ስለዚህ የቁጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አፈሰሰባቸው፤ በዙሪያቸውም አነደደው፤ እነርሱ ግን አላወቁም፥ አቃጠላቸውም እነርሱ ግን ልብ አላሉም።
ስለዚህ “ጠብቁኝ” ይላል ጌታ፤ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ፥ ፍርዴ ሕዝቦችን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነው፥ ይህም መዓቴንና የቁጣዬን ትኩሳት ሁሉ ለማፍሰስ ነው፤ በቅንዓቴ እሳት ምድርም ሁሉ ትበላለችና።