እግዚአብሔርስ ማዘኑን ረሳን? በቁጣውስ ርኅራኄውን ዘጋውን?
እኔም፣ “የልዑል ቀኝ እጅ እንደ ተለወጠ ማሰቤ፣ ይህ ድካሜ ነው” አልሁ።
ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! እኔን ያስጨነቀኝ በታላቁ ኀይልህ እኛን ከመርዳት ማቆምህ ነው።
የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁምና፥ በሕጉም ለመሄድ እንቢ አሉ፤
ያለ እውቀት ምክርን የሚሰውር ማን ነው? ስለዚህ እኔ የማላስተውለውን፥ የማላውቀውንም ድንቅ ነገር ተናግሬአለሁ።
እኔም ከድንጋጤዬ የተነሣ፦ “ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው አልሁ”።
በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምሕረቱን በእኔ የገለጠ ጌታ ይመስገን።
እኔ የተናቅሁ ነኝ አላወቅሁምም፥ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
ዐይኖቼ እንዲተጉ ያዝሃቸው፥ ስለተረበሽኩ አልተናገርሁም።
ቀኝህ ጌታ ሆይ፥ በኃይል ታላቅ ነው፤ አቤቱ፥ ቀኝህ ጌታ ሆይ፥ ጠላትን አደቀቀ።
ከሰማይ ተመልከት፥ ከቅዱስነትህና ከክብርህም ማደሪያ ጐብኝ፤ ቅንዓትህና ኃይልህስ ወዴት ነው? ለእኔም የሆነው የልብህ ናፍቆትና ርኅራኄህ ለእኔ ተከለከለ?
ወዲያውኑ የልጁ አባት፥ “አምናለሁ፤ አለማመኔን አይተህ እርዳኝ” በማለት ጮኸ።
ወይስ በፈተና፥ በተአምራት፥ በድንቅ፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራም ኃይል፥ በዐይናችሁ ፊት ጌታ አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ፥ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?