ቀንዳችሁን እስከ ላይ አታንሡ፥ በእብሪተኛ አንገት አትናገሩ።
ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፣ ወይም ከምድረ በዳ አይመጣምና፤
ፍርድ ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ፥ ወይም ከምድረ በዳ አይመጣም፤
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ሁሉ አንቀላፉ።
በደንዳና አንገቱና በወፍራሙ ጋሻው እየገሠገሠ ወደ እርሱ ይመጣበታልና፥
ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦ አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።
በኃይሉ ለዘለዓለም ይገዛል፥ ዐይኖቹ ወደ አሕዛብ ይመለከታሉ፥ ዓመፀኞች ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያድርጉ።
እኔ እብሪቱን አውቃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ፉከራው ሐሰት ነው፥ ሥራውም ሐሰት ነው።