መዝሙር 73:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሞታቸው ስቃይ የለውምና፥ ሰውነታቸውም ጤናማ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳች ጣር የለባቸውም፤ ሰውነታቸውም ጤናማና የተደላደለ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ምንም ሕመም ስለሌለባቸው፥ ሰውነታቸው ጤናማና ወዛም ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶችህ በበዓልህ መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ። |
አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።
በሚመጣው ዘመን ነገር ሁሉ የተረሳ ይሆናልና ለዘለዓለም የሚሆን የጠቢብና የአላዋቂ መታሰቢያ አይገኝም። አዬ ጉድ! ጠቢብ ከአላዋቂ ጋር እንዴት ይሞታል!
ወፍረዋል ሰብተዋልም፥ ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል፤ የድሀ አደጎች ነገር መልካም እንዲሆንላቸው አልተምዋገቱላቸውም፥ የችግርተኞችንም ፍርድ አልፈረዱላቸውም።