መዝሙር 7:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም ላደረጉልኝም ክፉን መልሼላቸው ከሆነ፥ ጠላቴንም በከንቱ ገፍቼው ከሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቴ አሳድዶ ይያዘኝ፤ ሕይወቴን ከምድር ይቀላቅል፤ ክብሬንም ከዐፈር ይደባልቅ። ሴላ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቴ አሳዶ ይያዘኝ! እስከ ሞት ድረስ ይርገጠኝ በአቧራም ላይ ጥሎ ክብር ያሳጣኝ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት፤ ያግኛትም፥ ሕይወቴን በምድር ላይ ይርገጣት፤ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርደው። |
ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።
“መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቁጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ።
በአንድ ላይም እንደ ጦረኞች ይሆናሉ፥ ጠላቶቻቸውንም በመንገድ ጭቃ ውስጥ የሚረግጡ ይሆናሉ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ስለሆነ ጦርነት ይገጥማሉ፥ ፈረሰኞችንም ያሳፍራሉ።
በዛሬው ዕለት በዋሻው ውስጥ ጌታ አንተን እንዴት አድርጎ በእጄ ላይ እንደጣለህ እነሆ በገዛ ዓይንህ አይተሃል፤ አንዳንዶች እንድገድልህ ገፋፍተውኝ ነበር፤ እኔ ግን፥ ‘ጌታ በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ በማለት ራራሁልህ።