መዝሙር 69:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ችግረኞች ያያሉ ደስ ይላቸዋል፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ ሕያዋንም ሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ድኾችን ይሰማልና፤ በእስራት ያለውንም ሕዝቡን አይንቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የችግረኞችን ጩኸት ይሰማል፤ በእስር ቤት ያሉትን ወገኖቹንም ችላ አይላቸውም። |
እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለች፤ እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል ጌታ። ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።
በዮሴፍ ቤት ላይ እንደ እሳት በድንገት እንዳይቀጣጠል፥ በቤቴልም ላይ የሚያጠፋው ሳይኖር እንዳይበላት፥ ጌታን ፈልጉ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ።
“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች መልካም ዜናን እንዳበሥር ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዐይነ ስውሮችም ማየትን እንዳውጅ፥ የተጨቆኑትንም ነጻ እንዳወጣ
የሚጠብቅህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያስገባ ነው፤ ለዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።