Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 69:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እግዚአብሔር ድኾችን ይሰማልና፤ በእስራት ያለውንም ሕዝቡን አይንቅም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ችግረኞች ያያሉ ደስ ይላቸዋል፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ ሕያዋንም ሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እግዚአብሔር የችግረኞችን ጩኸት ይሰማል፤ በእስር ቤት ያሉትን ወገኖቹንም ችላ አይላቸውም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 69:33
20 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ፤ የተገፉትን ምኞት ትሰማለህ፤ ልባቸውን ታበረታለህ፤ ጆሮህንም ወደ እነርሱ ጣል ታደርጋለህ፤


እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ ልመናቸውንም አይንቅም።


ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣ ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።”


አንዳንዶቹ በብረት ሰንሰለት ታስረው የተጨነቁ፣ በጨለማ፣ በጥልማሞት ውስጥ የተቀመጡ ነበሩ፤


እግዚአብሔር፣ “ስለ ችግረኞች መከራ፣ ስለ ድኾችም ጩኸት፣ አሁን እነሣለሁ፤ በናፈቁትም ሰላም አኖራቸዋለሁ” ይላል።


ለተበደሉት የሚፈርድ፣ ለተራቡት ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ እግዚአብሔር እስረኞችን ከእስራት ያወጣል፤


የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስታውሳሉ፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ፤ የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ፣ በፊቱ ይሰግዳሉ።


ኑና ከእኔ ጋራ እግዚአብሔርን አክብሩት፤ ስሙንም በአንድነት ከፍ ከፍ እናድርግ።


ይህ ችግረኛ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።


እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤተ ሰብ መካከል ያኖራል፤ እስረኞችን ነጻ አውጥቶ ያስፈነድቃል፤ ዐመፀኞች ግን ምድረ በዳ ይኖራሉ።


እነዚህን ነገሮች ሁሉ እጄ አልሠራችምን? እንዲገኙስ ያደረግሁ እኔ አይደለሁምን?” ይላል እግዚአብሔር። “ነገር ግን እኔ ወደዚህ፣ ትሑት ወደ ሆነና መንፈሱ ወደ ተሰበረ፣ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።


እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህ ይላል፤ “እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።


እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ አለዚያ እንደ እሳት የዮሴፍን ቤት ያወድማል፤ እሳቱም ቤቴልን ይበላል፤ የሚያጠፋውም የለም።


“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እርሱ ቀብቶኛልና፤ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንዳወጣ፣


በዚህም ምክንያት እኔ ጳውሎስ ለእናንተ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ሆኛለሁ።


ሊደርስብህ ያለውን መከራ አትፍራ። እነሆ፤ ዲያብሎስ ሊፈትናችሁ አንዳንዶቻችሁን ወደ እስር ቤት ይጥላል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos