መዝሙር 64:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፥ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፥ ማንስ ያየናል? ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግፍን ያውጠነጥናሉ፤ ደግሞም፣ “የረቀቀች ሤራ አዘጋጅተናል” ይላሉ፤ አቤት! የሰው ልቡ፣ አእምሮውም እንዴት ጥልቅ ነው! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ክፉ ዕቅድ ዐቀዱ፤ “በሐሳባቸውም የተቀናጀ ወንጀል እንሠራለን” ይላሉ፤ ይህም የሰው ልብና የሰው አእምሮ በተንኰል የተሞላ መሆኑን ያሳያል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀይልህ ተራሮችን አጸናሃቸው፥ እነርሱም በኀይል ታጥቀዋል። |
ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።
ነገር ግን እዚያ ከነበሩት የሳኦል አገልጋዮች ጋር ቆሞ የነበረው ኤዶማዊው ዶይቅ እንዲህ አለ፥ “የእሴይ ልጅ በኖብ ወዳለው ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ አቢሜሌክ ሲመጣ አይቻለሁ።
ከዚያም ዳዊት ከዋሻው ወጥቶ ሳኦልን፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጠራው። ሳኦልም ወደ ኋላው ዞር ባለ ጊዜ፥ ዳዊት ወደ መሬት ጐንበስ ብሎ እጅ ሲነሣው ተመለከተ፤
ናባልም ለዳዊት አገልጋዮች እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ለመሆኑ ይህ ዳዊት ማነው? የእሴይስ ልጅ ማን ነው? በአሁኑ ጊዜ ከጌቶቻቸው የሚኰበልሉ አገልጋዮች ብዙ ናቸው።