መዝሙር 63:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኤዶምያስ ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ከልብ እሻለሁ፤ ውሃ በሌለበት፣ በደረቅና በተራቈተ ምድር፣ ነፍሴ አንተን ተጠማች፤ ሥጋዬም አንተን ናፈቀች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደ ተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ወደ አንተ የለመንሁትን ጸሎቴን ስማኝ፥ ከጠላትም ጥርጥር ነፍሴን አድናት። |
ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ ሕዝቡም በሙሴ ላይ አጉረመረሙ “እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብጽ አወጣኸን?” አሉ።
ሰውም ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፥ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፥ በበረሃም አገር እንደ ትልቅ ቋጥኝ ጥላ ይሆናል።
በወናዎቹ ኮረብቶች ላይ ወንዞችን፥ በሸለቆዎችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ ማከማቻ፥ የጥማትንም ምድር ለውሃ መፍለቂያ አደርጋለሁ።
ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።
ኢየሱስም “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ‘እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ፤’ ብለሽ ንገሪአቸው፤” አላት።
ይሁን እንጂ ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፥ “በዐምባው ውስጥ አትቆይ፤ ሂድና ወደ ይሁዳ ምድር ግባ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ።