ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ።
ምግብ ፍለጋ ይንከራተታሉ፣ ካልጠገቡም ያላዝናሉ።
እነርሱ ምግብ ለማግኘት እንደሚቅበዘበዙና በቂ ምግብ ካላገኙም እንደሚያላዝኑ ውሾች ናቸው።
ተቅበዝብዞም፦ ወዴት አለ? እያለ እንጀራ ይለምናል፥ የጨለማ ቀን እንደ ቀረበበት ያውቃል።
ልጆቹም እጅጉን ይቅበዝበዙ፥ ይለምኑም፥ ከፈራረሱ ቤቶቻቸውም ሳይቀር ይባረሩ።
መብል የሚወዱ ከቶ የማይጠግቡ ውሾች ናቸው፤ እረኞቹም ማስተዋል የማይችሉ ናቸው፤ ሁሉም ወደ መንገዳቸው ዞሩ፥ ከፊተኛው እስከ ኋለኛው ድረስ ሁሉ፥ እያንዳንዳቸው ወደ ጥቅማቸው ዘወር ብለዋል።
ተጨንቀውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ክፉኛ ሲራቡም ይቈጣሉ፤ ወደ ላይ እየተመለከቱ ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይራገማሉ።
ከምድረበዳ ሰይፍ የተነሣ በሕይወታችን እንጀራችንን እናመጣለን።
ጌታ ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፦ ሰው ሲያበላቸው “ሰላም አለ” ይላሉ፤ ካላበላቸው ግን ጦርነት ሊያውጁበት ይነሣሉ።
ጌታ የሚያስነሣብህን ጠላቶችህን ታገለግላለህ፤ በራብና በጥማት፥ በእርዛትና በማጣት እስኪያጠፉህም ድረስ በዐንገትህ ላይ የብረት ቀንበር ይጭኑብሃል።