ኢሳይያስ 56:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 መብል የሚወዱ ከቶ የማይጠግቡ ውሾች ናቸው፤ እረኞቹም ማስተዋል የማይችሉ ናቸው፤ ሁሉም ወደ መንገዳቸው ዞሩ፥ ከፊተኛው እስከ ኋለኛው ድረስ ሁሉ፥ እያንዳንዳቸው ወደ ጥቅማቸው ዘወር ብለዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 እጅግ ሲበዛ ሆዳም ውሾች ናቸው፤ ጠገብሁን አያውቁም፤ የማያስተውሉ እረኞች ናቸው፤ ሁሉም በየራሳቸው መንገድ ሄዱ፤ እያንዳንዳቸውም የግል ጥቅማቸውን ፈለጉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 እነርሱ በልተው እንደማይጠግቡ ውሾች ናቸው። የማያስተውሉም እረኞች ናቸው፤ ሁሉም በየራሳቸው መንገድ ይሄዳሉ፤ እያንዳንዱም የራሱን ጥቅም ያሳድዳል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ሁሉም ከቶ የማይጠግቡ የረከሱ ውሾች ናቸው፤ እነርሱም ያስተውሉ ዘንድ የማይችሉ ክፉዎች ናቸው፤ ሁሉም እያንዳንዳቸው እንደ ፈቃዳቸው መንገዳቸውን ተከትለዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 መብል ወዳጆች ከቶ የማይጠግቡ ውሾች ናቸው፥ እነርሱም ያስተውሉ ዘንድ የማይችሉ እረኞች ናቸው፥ ሁሉ ወደ መንገዳቸው፥ ከፊተኛው እስከ ኋለኛው ድረስ ሁሉ፥ እያንዳንዳቸው ወደ ጥቅማቸው ዘወር ብለዋል። Ver Capítulo |