መዝሙር 58:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። የዳዊት ቅኔ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀያላን ሆይ፤ በውኑ ጽድቅ ከአፋችሁ ይወጣል? የሰው ልጆች ሆይ፤ በቅን ትፈርዳላችሁን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ገዢዎች! በትክክል ትናገራላችሁን? በሰዎችስ መካከል ያለ አድልዎ ትፈርዳላችሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላኬ ሆይ፥ ከጠላቶች አድነኝ፤ በላዬም ከቆሙት አስጥለኝ። |
ስለዚህም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም ኬብሮን ላይ በጌታ ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ እነርሱም በእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን ቀቡት።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በሕዝቡ ላይ ሽማግሌዎችና አለቆች እንደ ሆኑ የምታውቃቸውን የእስራኤል ሽማግሌዎች የሆኑ ሰባ ሰዎች ሰብስብልኝ፤ እነርሱንም ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣቸው፥ በዚያም ከአንተ ጋር በየቦታቸው ይቁሙ።
በሰሙም ጊዜ ማልደው ወደ መቅደስ ገብተው አስተማሩ። ግን ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጥተው ሸንጎውንና የእስራኤልን ልጆች ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ጠሩ፤ ያመጡአቸውም ዘንድ ወደ ወኅኒ ላኩ።