በቀንና በሌሊት በቅጥርዋ ይከብቡአታል፥ በደልና ሁከት በመካከልዋ ነው፥
ጥፋት በመካከሏ ይገኛል፤ ግፍና አታላይነትም ከጐዳናዋ አይጠፋም።
በከተማዋ ውስጥ ጥፋት አለ፤ አደባባዮችዋም በጭቈናና በአታላይነት የተሞሉ ናቸው።
በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?
አፉ በመርገም፥ በሽንገላና በዐመፃ የተመላ ነው፥ ከምላሱ በታች ተንኰልና ክፋት አሉ።
አቤቱ፥ በጠላቶቼ ምክንያት በጽድቅህ ምራኝ፥ መንገዴን በፊትህ አቅና።
ድሮቻቸውም ልብስ አይሆኑላቸውም፥ ራሳቸውንም በሠሩት መሸፈን አይችሉም፤ ሥራቸውም የበደል ሥራ ነው፥ የግፍም ሥራ በእጃቸው ነው።
እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፥ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው፥ ጉስቁልናና ውድመት በሚሄዱበት አለ።
ኢየሱስን በተንኰል ይዘው ሊገድሉት ተማከሩ፤