እግዚአብሔርን ረዳቱ ያላደረገ፥ በሀብቱም ብዛት የታመነ፥ በከንቱ ነገርም የበረታ ያ ሰው እነሆ።
ስላደረግኸው ነገር ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤ ስምህ መልካም ነውና፣ ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ፤ በቅዱሳንም መካከል አመሰግንሃለሁ።
አምላክ ሆይ! ስላደረግኸው መልካም ነገር ሁሉ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ፤ በአማኞች ፊት ቆሜ ስለ አንተ ቸርነት እናገራለሁ።
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ጌታን አመሰግናለሁ፥ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
በጌታ ተስፋ አድርግ፥ በርታ፥ ልብህም ይጽና፥ በጌታ ተስፋ አድርግ።
ልቅሶዬን ወደ እልልታ ለወጥህልኝ፥ ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ።
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
እነሆ፥ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ ጌታም ለሕይወቴ ደጋፊ ነው።
ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የዳዊት መዝሙር
ከከፍታ ያናውጡት ዘንድ መከሩ፥ ሐሰትንም ይወድዳሉ፥ በአፋቸው ይባርካሉ፥ በልባቸውም ይረግማሉ።
ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፥ መጠለያዬም ጌታ ነው ሥራህን ሁሉ እናገር ዘንድ።
የጌታ ስም የጸና ግምብ ነው፥ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።