መዝሙር 5:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፥ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እብሪተኞች በፊትህ መቆም አይችሉም፤ ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ ጠላህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢተኞች በፊትህ አይቆሙም፤ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ትጠላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐመፀኞችም በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ ዐመፅ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ። |
ክፋታቸው ሁሉ በጌልገላ አለ፤ በዚያ ሳሉ ጠላኋቸው፤ ስለ ሥራዎቻቸውም ክፋት ከቤቴ አስወጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመፀኞች ናቸው።
ዐይኖችህ ክፉ እንዳያዩ እጅግ ንጹሐን ናቸው፥ ክፉ ሥራም መመልከት አትችልም፤ አታላዮችን ለምን ትመለከታለህ? ክፉዎቹ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆኑትን ሲውጡ ለምን ዝም ትላለህ?
ከዚህ በኋላ በግራው ያሉትን ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ።