ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል።
ሰው ባለጠጋ ሲሆን፣ የቤቱም ክብር ሲበዛለት አትፍራ፤
ሰው ሀብታም ሲሆን፥ የቤቱም ብልጽግና እየበዛ ሲሄድ አትፍራው፤
ኀጢአተኛውን ግን እግዚአብሔር አለው፦ “ለምን አንተ ሕጌን ትናገራለህ? ኪዳኔንም በአፍህ ለምን ትወስዳለህ?
ያዕቆብም፥ የላባ ልጆች፦ “ያዕቆብ የአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ፥ የአባታችን ከነበረውም ይህንም ሁሉ ሀብት አገኘ” ሲሉ ሰማ።
የዳዊት መዝሙር። በክፉዎች ላይ አትቅና፥ ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፥
በጌታ ጽና በተዕግሥትም ጠብቀው። መንገዱም በቀናችለትና በሚያደባ ሰው አትቅና።
ጆሮዬን ወደ ምሳሌዎች አዘነብላለሁ፥ በበገናም ምሥጢሬን እገልጣለሁ።
ጻድቃን ድል ባደረጉ ጊዜ ብዙ ክብር አለ፥ ክፉዎች ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ ግን ሰው ይሸሸጋል።
ከሲኦል እጅ እታደጋቸዋለሁ፥ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤ ሞት ሆይ! ቸነፈርህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! አጥፊነትህ ወዴት አለ? ርኅራኄ ከዓይኔ ተሰወረች።
አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፤ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርሷ ያመጣሉ፤
የአሕዛብንም ግርማና ክብር ወደ እርሷ ያመጣሉ።