ከእነርሱም አንዱ ሴዴቅያስ ተብሎ የሚጠራው የከናዕና ልጅ ከብረት የተሠሩ ቀንዶችን ይዞ አክዓብን “ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘ከብረት በተሠሩ በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’” አለው።
መዝሙር 44:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ፥ ለያዕቆብ መድኃኒትን እዘዝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንተ ጠላቶቻችን በመጡበት እንዲመለሱ እናደርጋለን፤ በስምህም ባላጋራዎቻችንን ከእግራችን በታች እንረግጣለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንተ ርዳታ ጠላቶቻችንን ድል እንነሣለን፤ በስምህም ተቃዋሚዎቻችንን እንረግጣለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያል ሆይ፥ ፍላጻዎችህ የተሳሉ ናቸው፥ አሕዛብ በበታችህ ይወድቃሉ። በንጉሥ ጠላቶች ልብ ውስጥ ይገባሉ፥ |
ከእነርሱም አንዱ ሴዴቅያስ ተብሎ የሚጠራው የከናዕና ልጅ ከብረት የተሠሩ ቀንዶችን ይዞ አክዓብን “ጌታ እንዲህ ይላል፤ ‘ከብረት በተሠሩ በእነዚህ ቀንዶች ሶርያውያንን ወግተህ ፍጹም የሆነ ድልን ትቀዳጃለህ’” አለው።
በአንድ ላይም እንደ ጦረኞች ይሆናሉ፥ ጠላቶቻቸውንም በመንገድ ጭቃ ውስጥ የሚረግጡ ይሆናሉ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ስለሆነ ጦርነት ይገጥማሉ፥ ፈረሰኞችንም ያሳፍራሉ።
ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፥ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፥ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፥ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።”