መዝሙር 44:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰይፋቸው ምድርን አልወረሱም ክንዳቸውም አላዳናቸው፥ ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፥ ወድደሃቸዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ንጉሤ ነህ፤ ያዕቆብም ድል እንዲያደርግ የወሰንህ አንተ ነህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ንጉሤና አምላኬ ነህ፤ የያዕቆብ ዘር ለሆነው ሕዝብህ፥ ድልን የምታጐናጽፍ አንተ ነህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም አቅና፥ ተከናወን፥ ንገሥም፤ ቀኝህም በክብር ይመራሃል። |
ኢየሱስም ሕዝቡ ወደዚያ እየተንጋጋ በሩጫ መምጣታቸውን ባየ ጊዜ፥ “አንተ ደንቆሮና ዲዳ መንፈስ ከእርሱ ውጣ! ከእንግዲህም ተመልሰህ እንዳትገባበት አዝዤሃለሁ” ብሎ ርኩሱን መንፈስ ገሠጸው።
ዓይንህ ያየችውን ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ ጌታ አምላክህ ሲያስወጣህ የጸናችውን እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ፥ እንደዚሁ ሁሉ ጌታ አምላክህ አንተ በምትፈራቸው በሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደርጋል።
ነገር ግን ጌታ ስለ ወደዳችሁ፥ አባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አወጣችሁ።