በከንቱ ያጠፉኝ ዘንድ ወጥመዳቸውን ሸሽገውብኛልና፥ ነፍሴን በከንቱ አበሳጭተዋልና።
ያለ ምክንያት ወጥመዳቸውን በስውር አስቀምጠውብኛልና፤ ያለ ምክንያት ለነፍሴ ጕድጓድ ቈፍረውላታል።
ያለ ምክንያት ወጥመድ በድብቅ ዘርግተውብኛል፤ እኔንም ለመያዝ ጒድጓድ ቆፍረዋል።
አቤቱ፥ ሰውንና እንስሳን ታድናለህ። አቤቱ፥ ምሕረትህን እንደ አበዛህ፥ የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ።
እግሩ በወጥመድ ትያዛለች፥ በመረብም ላይ ይሄዳል።
ኃጢአተኞች ጉድጓድ ቆፈሩልኝ፥ አቤቱ፥ እንደ ሕግህ ግን አይደለም።
አቤቱ፥ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፥ እርምጃዬንም ሊያሰናክሉ ከመከሩ ከዓመፀኞች አድነኝ።
አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፥ በከንቱ የሚከዱ ያፍራሉ።
ለእግሮቼ ወጥመድን አዘጋጁ፥ ነፍሴንም አጐበጡአት፥ ጉድጓድ በፊቴ ቈፈሩ፥ በእርሱም ወደቁ።
እንደ ሰይፍ ምላሳቸውን አሰሉ፥ እንደ ፍላጻ መራራ ነገርን ለመወርወር፥
በጩኸት ደከምሁ ጉሮሮዬም ሰለለ፥ አምላኬን ስጠብቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ።
ምስጋናውን ሁሉ እናገር ዘንድ፥ በጽዮን ልጅ በደጆችዋ በማዳንህ ደስ ይለኛል።
ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ።
ነገር ግን በሕጋቸው ‘በከንቱ ጠሉኝ’ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።