ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።
መዝሙር 35:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴን ሊያጠፉ የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐስቁሉም፥ ክፉትን በእኔ ላይ የሚያስቡ ይዋረዱ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕይወቴን የሚፈልጓት፣ ይቅለሉ፣ ይዋረዱ፤ እኔን ለማጥፋት የሚያሤሩ፣ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን ለመግደል የሚፈልጉ ሁሉ ኀፍረትና ውርደት ይድረስባቸው! በእኔ ላይ የሚያሤሩም ሁሉ ተዋርደው ወደ ኋላቸው ይመለሱ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመኝታው ዐመፅን ዐሰበ፤ በሁሉ ነገር መልካም ባልሆነች መንገድ ቆሞአል፤ ክፋትንም አይሰለቻትም። |
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።
ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኃያላኖቻቸውም ሲደበደቡ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዚህና በዚያ ድንጋጤ አለ፥ ይላል ጌታ።
እፍኝ ገብስና ቁራሽ እንጀራ ለማግኘት ብላችሁ፥ ውሸት ለሚሰሙት ሕዝቤ እየዋሻችሁ፥ ሞት የማይገባቸውን ነፍሳት በመግደል፥ በሕይወትም መኖር የማይገባቸውን ነፍሳት በሕይወት በማትረፍ በሕዝቤ ፊት አርክሳችሁኛል።
ስለዚህ የሚደበቅባቸውን ቦታዎች ሁሉ ካያችሁ በኋላ ግልጽ መረጃ ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አብሬችሁ እሄዳለሁ፤ ብቻ በዚያ አገር ይገኝ እንጂ በይሁዳ ነገዶች ሁሉ መካከል ከገባበት ጉድጓድ ገብቼ አወጣዋለሁ።”