የሐሰት ምስክሮች ተነሡብኝ፥ የማላውቀውንም በእኔ ላይ ተናገሩ።
ጨካኝ ምስክሮች ተነሡ፤ ስለማላውቀውም ነገር ጠየቁኝ።
ክፉ ሰዎች ባልሠራሁት ወንጀል ከሰሱኝ፤ በማላውቀውም ነገር በሐሰት መሰከሩብኝ።
የትዕቢት እግር አይምጣብኝ፥ የኀጢአተኛ እጅም አያውከኝ።
የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ።
“ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤
ከዚያም ዳዊት ከዋሻው ወጥቶ ሳኦልን፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጠራው። ሳኦልም ወደ ኋላው ዞር ባለ ጊዜ፥ ዳዊት ወደ መሬት ጐንበስ ብሎ እጅ ሲነሣው ተመለከተ፤
ናባልም ለዳዊት አገልጋዮች እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ለመሆኑ ይህ ዳዊት ማነው? የእሴይስ ልጅ ማን ነው? በአሁኑ ጊዜ ከጌቶቻቸው የሚኰበልሉ አገልጋዮች ብዙ ናቸው።