ምድር ሁሉ ጌታን ትፍራው፥ በዓለም የሚኖሩ ሁሉ ይደንግጡ።
ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፤ በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ።
በምድርም የምትኖሩ ሁሉ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔርን አክብሩ።
እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ፥ ዕወቁም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ብፁዕ ነው።
ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል፥ በልባቸውም ጠቢባን የሆኑትን ሁሉ አይመለከትም።”
ችግረኞች ይበላሉ፥ ይጠግቡማል፥ ጌታንም የሚሹት ያመሰግኑታል፥ ልባቸውም ለዘለዓለም ሕያው ይሁን።
ምድር ፍሬዋን ሰጠች፥ እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል።
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ፈረሶች አንቀላፉ።
አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።