ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጉሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።
በልባብና በልጓም ካልተገሩ በቀር፣ ወደ አንተ እንደማይቀርቡት፣ ማስተዋል እንደሌላቸው፣ እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።
እንዲገቱ ለማድረግ በልባብና በልጓም እንደሚመሩት እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ የማይገባችሁ አትሁኑ። እንደዚያ ካላደረጋችሁ ፈረስና በቅሎ ወደ እናንተ አይቀርቡም።
እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑ፤ እርሱ አዘዘ፤ ተፈጠሩም።
የቀስቴን አውታር አላልቶብኛል፥ አዋርዶኝማል፥ እነርሱም በፊቴ ልጓማቸውን ፈትተዋል።
እስትንፋሱ ከሰልን ታቃጥላለች፥ ነበልባልም ከአፉ ይወጣል።
አለንጋ ለፈረስ፥ ልጓም ለአህያ፥ በትርም ለሞኝ ጀርባ ነው።
በእውነት ኤፍሬም ሲያለቅስ ሰማሁ፦ ‘ቀጣኸኝ እኔም እንዳልተገራ ወይፈን ተቀጣሁ፤ አንተ ጌታ አምላኬ ነህና መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ።
“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”
ፈረሶች እንዲታዘዙልን ልጓም በአፋቸው ውስጥ እናስገባለን፤ መላ ሰውነታቸውንም መምራት እንችላለን።