መዝሙር 29:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፥ ጌታ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤ የእግዚአብሔር ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ድምፅ በረሓን ያናውጣል፤ የቃዴስንም በረሓ ያንቀጠቅጣል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ወደ አምላኬም ለመንሁ። |
ጌታም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ያሰማል፥ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፥ ጌታ ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፥ ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።
ተጉዘውም በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ መጡ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።
ያንጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጧት ነበር፤ አሁን ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም፤” ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል።