የቸርነትህን ብዛት መታሰብ ያወጣሉ፥ በጽድቅህም ሐሤትን ያደርጋሉ።
የበጎነትህን ብዛት በደስታ ያወሳሉ፤ ስለ ጽድቅህም በእልልታ ይዘምራሉ።
ስለ ደግነትህ ገናናነት ይናገራሉ፤ ስለ ጽድቅህ ኀይል ከፍ ባለ ድምፅ ይዘምራሉ።
ለተበደሉትም የሚፈርድላቸው፥ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ ነው። እግዚአብሔር የታሰሩትን ይፈታቸዋል፤
የሕይወት ምንጭ በአንተ ዘንድ ነውና፥ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።
የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።
አቤቱ፥ ጽድቅህ እስከ አርያም ይደርሳል፥ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፥ አምላክ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
እልልታ የሚያውቅ ሕዝብ ብፁዕ ነው፥ አቤቱ፥ በፊትህ ብርሃን ይሄዳሉ።
ጌታ ስላደረገልን ሁሉ፥ የጌታን ቸርነትና የጌታን ምስጋና፥ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን የተትረፈረፈ ጽኑ ፍቅር እናገራለሁ።
በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም በደኅንነት ይቀመጣል፥ እርሱም፦ ‘ጌታ ጽድቃችን ነው’ በሚለው በዚህ ስም የሚጠራ ይሆናል።