መዝሙር 142:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ቀኝ ተመለከትሁ አየሁም፥ የሚያውቀኝም አጣሁ፥ መሸሸጊያም የለኝም፥ ስለ ነፍሴም የሚያስብ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ጠባቂዬ አንተ ነህ፤ በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ አንተ ነህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀድሞውን ዘመን ዐሰብሁ፥ ሥራህንም ሁሉ አነበብሁ፤ የእጅህንም ሥራ አነብባለሁ። |
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ፥ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፥ በሚገፉአቸውም እጅ ኃይል ነበረ፥ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።
እነሆ፥ እያንዳንዳችሁ ወደ ቤት የምትበታተኑበት እኔንም ለብቻዬ የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፤ አሁንም ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።