እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
እስራኤልንም በመካከሉ አሳለፈ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
ቀይ ባሕርን ገሠጸው፥ እርሱም ደረቀ፥ እንደ ምድረ በዳ በጥልቁ መራቸው።
ባሕርን ከፍሎ አሳለፋቸው፥ ውኆችን እንደ ግንብ አቆመ።
የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ መካከል በደረቅ ምድር ሄዱ፤ ውኃውም በቀኛቸውና በግራቸው ግድግዳ ሆነላቸው።