14 እስራኤልንም በመካከሉ አሳለፈ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
14 እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
14 እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
ቀይ ባሕርን በገሠጸው ጊዜ ደረቀ፤ ጥልቁን ውሃ እንደ በረሓ አድርጎ ሕዝቦቹን እየመራ አሻገራቸው።
ባሕሩን ከፍሎ በመካከሉ አሳለፋቸው፤ ውሃው እንደ ግንብ እንዲቆም አደረገ።
እስራኤላውያንም በደረቅ ምድር ባሕሩን ተሻግረው ሄዱ፤ ውሃውም በግራና በቀኝ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበር።