መዝሙር 135:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ያዕቆብን ለራሱ፥ እስራኤልንም ግዛቱ አድርጎ መርጦታልና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፣ እስራኤልንም ውድ ንብረቱ አድርጎ መርጧልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፥ የእስራኤልንም ሕዝብ የግሉ አድርጎ መረጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ብቻውን ታላቅ ተአምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤ |
ብቻ ጌታ ስለ አባቶችህ ደስ ብሎታል፥ እነርሱንም ወድዶአል፥ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራቸውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መረጠ።
መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።