ዕዝራም ታላቁን አምላክ ጌታን ባረከ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን በመዘርጋት፦ አሜን፥ አሜን ብለው መለሱ። ራሳቸውን አዘነበሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ለጌታ ሰገዱ።
መዝሙር 134:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌሊት በቤተ መቅደስ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፥ ጌታንም ባርኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመቅደሱ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፤ እግዚአብሔርንም ባርኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመቅደሱ እጆቻችሁን ለጸሎት ዘርግታችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ፥ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ። |
ዕዝራም ታላቁን አምላክ ጌታን ባረከ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን በመዘርጋት፦ አሜን፥ አሜን ብለው መለሱ። ራሳቸውን አዘነበሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ለጌታ ሰገዱ።
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፥ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች በደረቅ መሬት፥ ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።
ቆፍ። ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፥ በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።