አቤቱ፥ ለመልካሞች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም ለሆኑ፣ ልባቸውም ለቀና መልካም አድርግ።
እግዚአብሔር ሆይ! ትእዛዞችህን ለሚፈጽሙ ደጋግ ሰዎች ቸርነት አድርግላቸው።
አቤቱ፥ በአዜብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ።
አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥ በቸርነትህም ሥርዓትህን አስተምረኝ።
እንዳላፍር ልቤ በሥርዓትህ የቀና ይሁን።
ጌታ በደልን የማይቈጥርበት በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው ብፁዕ ነው።
የሕይወት ምንጭ በአንተ ዘንድ ነውና፥ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።
መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፥ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም።
የክፉዎች በደል ይጥፋ፥ ጻድቁን ግን አቅና፥ እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን ይመረምራል።
የአሳፍ መዝሙር። እግዚአብሔር ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው፥ ልባቸው ንጹሕ ለሆነ።
ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥ በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።
ጌታ አምላክ ፀሐይና ጋሻ ነው፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፥ ጌታ በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያስቀራቸውም።
ፍርድ ወደ ጽድቅ እስክትመለስ ድረስ ልበ ቅኖችም ሁሉ ይከተሉአታል።
ጤት። ጌታ በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።
ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ “ተንኰል የሌለበት እውነተኛ የእስራኤል ሰው እነሆ!” አለ።
እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።
በአፋቸውም ውሸት አልተገኘም፤ ነውር የለባቸውም።