መዝሙር 124:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቍጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፣ በቁመናችን በዋጡን ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በታላቅ ቊጣ በእኛ ላይ ተነሥተው ከነሕይወታችን በዋጡን ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቃን እጃቸውን በዐመፃ እንዳይዘረጉ እግዚአብሔር የኃጥኣንን በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይተውምና። |
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ፥ አደቀቀኝም፥ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፥ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፥ ከሚጣፍጠውም ምግቤ ሆዱን ሞላ፥ እኔንም አውጥቶ ተፋኝ።
ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፥ ወታደሮችን ልኮ ከሰብአ ሰገል በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን በቤተ ልሔምና በአካባቢዋ የነበሩትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።
በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ ከእርሱ ለመነ።