መዝሙር 122:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታን ስም ያመሰግኑ ዘንድ፥ ለእስራኤል ምስክር ሊሆኑ የጌታ ነገዶች ወደዚያ ይወጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእስራኤል በተሰጠው ሥርዐት መሠረት፣ የእግዚአብሔርን ስም ለማመስገን፣ የእግዚአብሔር ነገዶች ወደዚያ ይመጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትእዛዙ መሠረት ለእግዚአብሔር ምስጋና ለማቅረብ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ የሚሰበሰቡት ወደዚህች ከተማ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባለጠጎችን ስድብና የትዕቢተኞችን ውርደት ነፍሳችን እጅግ ጠገበች። |
ጌታ አምላካችሁም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራቶቻችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ እንዲሁም ለጌታ የተሳላችሁትን ምርጥ ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ታመጣላችሁ።
“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ በቂጣ በዓል፥ በመከርንና በዳስ በዓል፥ በአምላክህ በጌታ ፊት እርሱ በመረጠው ስፍራ ይታዩ፥ በጌታም ፊት ባዶ እጃቸውን አይታዩ።