መዝሙር 120:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፥ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሜሼኽ እኖራለሁና፣ በቄዳር ድንኳኖች መካከል እቀመጣለሁና ወዮልኝ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቄዳር ሕዝብ መካከል በሜሼክ ስደተኛ ሆኜ በመኖሬ ወዮልኝ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ይጠብቅህ፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጁ ይጋርድህ። |
በትውልዳቸው ቅደም ተከተል የተዘረዘሩት የእስማኤል የልጆቹ ስም እንዲህ ነው፥ የእስማኤል የበኩር ልጁ ነባዮት፥ እና ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥
እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የሙግትና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።
አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፦ አሁንም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሞሼኽና የቱባል አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፥
“የት እንደምትኖር አውቃለሁ፥ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ነው፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።
ሳሙኤልም ሞተ፤ መላው እስራኤል ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ ራማ ባለው ቤቱም ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ።