ስለ ሽንገላ አንደበት ምንን ይሰጡሃል? ምንስ ይጨምሩልሃል?
ሐሰተኛ አንደበት ሆይ፤ ምን ይከፈልህ? ከዚህስ የባሰ ምን ይደረግብህ?
እናንተ አታላዮች! እግዚአብሔር እናንተን ምን ቢያደርጋችሁ ይሻላል? እንዴትስ ቢቀጣችሁ ይሻላል?
ለእግሮችህ ሁከትን አይሰጣቸውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም።
እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በወሰደ ጊዜ፥ አምላክን የካደ ሰው ተስፋው ምንድነው?
ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?
ታዲያ አሁን ከምታፍሩበት ነገር ሌላ ያንጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የእነዚህ ነገሮች መጨረሻ ሞት ነውና።